Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከ400 መቶ ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ለማህበረስቡ ለማሰራጨት ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣መስከረም 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ400 መቶ ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ለማህበረሰቡ ለማሰራጨት ዝግጅት ማጠናቀቁን የደሴ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለጸ።
የመምሪያው ሀላፊ አቶ ዮናስ እንዳለ ለጣቢያችን እንደተናገሩት፥ መንግስት ከቀረጥ ነጻ ገብተው የኑሮ ወድነቱን መቀነስ የሚያስችሉ መሠረታዊ ፍጆታዎችን ለማህበረሰቡ ለማቅረብ ባቀደው መሠረት የደሴ ከተማ 400 መቶ ሺህ ሊትር ዘይት ለማህበረሰቡ ያከፋፍላል ብለዋል።
ዘይቱ ከወደብ ተጓጉዞ ኮምቦልቻ ከተማ መድረሱን የተናገሩት ሀላፊው፥ የሸማች ማህበራት በማጓጓዝ ለማህበረሰቡ ማከፍፈል ይችላሉ ብለዋል።
ከተማዋ የሚያስፈልጋት ከ8 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር በሚቀጥለው ሳምንት ይደርሳል ያሉት ሀላፊው፥ በዱቄት አቅርቦት በኩልም ከፍብሪካዎች ጋር በመነጋገር ምርት መጀመሩን ተናግረዋል።
ከተማዋ በርካታ ተፈናቃዮችን እያስተናገደች እንደመሆኑ መጠን በልዩ እንዲታይ ከክልሉ ጋር እየተሠራ ነው ብለዋል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.