Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስቅለትና የትንሳኤ በዓላት በሠላም እንዲከበሩ ዝግጅት ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስቅለትና የትንሳኤ በዓላት በሠላም እንዲከበሩ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ስራ መግባቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በኮሚሽኑ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር በላይነህ በቀለ እንደገለፁት፥ የስቅለትና የትንሳኤ በዓላት በክርስትና ዕምነት ተከታዮች በድምቀት ከሚከበሩ ሐይማኖታዊ በዓላት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።

በክልሉ በስድስቱም ዞኖችየፖሊስሀይሉከሌሎችየፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሰላም እንዲከበር የጋራ እቅድ በማውጣት ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

ከበዓሉ ጋርተያይዞ በሚኖረው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አደጋ እንዳይከሰት የትራፊክ ፖሊሶችን በማሰማራት አደጋን ለመከላከልና ለመቀነስ በቅርበት ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ማንኛውንም አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኝ የፀጥታ አካል ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበርም ኃላፊው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።

ረዳት ኮሚሽነር በላይነህ በበዓሉ ግብይት ወቅት ህብረተሰቡ በሀሰተኛ የብር ኖቶችና ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀሉ ምርቶችን በሚሸጡ አካላት እንዳይጭበረበር ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስገንዝበዋል።

በበዓል ወቅት ከሚፈጸሙ ወንጀሎች መካከል በተለይ በቅቤ፣ በርበሬና አይብ ላይ ባዕድ ነገር መቀላቀል እንደሚገኙበት ጠቁመው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.