Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ሱዳን  በእርስ በርስ ግጭት የ300 ሰዎች  ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በደቡብ ሱዳን በተቀሰቀሰ የእርስ በእርስ ግጭት የ300 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
 
በሀገሪቱ በስተምሥራቅ በጆንግሌይ ግዛት በቅርቡ በተቀሰቀሰው ግጭት ሕይወታቸው ካለፈው 300 ሰዎች መካከል ሶስት የእርዳታ ሰጪ ሰራተኞች ይገኙበታል ነው ያሉት።
 
ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ በርካቶች መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
 
ግጭቱ ቅዳሜ ዕለት በሙርሌ እና በሉዊ ኑር ማህበረሰቦች መካከል የተጀመረ ሲሆን የሞርሌ ወጣቶች በኡሮር አውራጃ ብዙ መንደሮችን ማቃጠላቸውን የአከባቢው ሽማግሌዎች ተናግረዋል።
 
በአካባቢው የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው፥ የጥቃቱ ሰለባዎች አብዛኛዎቹ በጥይት የተጎዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
 
ከዚያም ባለፈ ከተጎዱት መካከል የተወሰኑት ለህክምና ወደ ዋና ከተማዋ ጁባ በአውሮፕላን ተወስደዋልም ነው ያሉት።
 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግጭቱ ወደ ተቀሰቀሰበት አካባቢ የሰላም አስከባሪ ቡድን ማሰማራቱ ተነግሯል።
 
የሀገሪቱ ባለስልጣናት በየካቲት ወር ከተቀሰቀሰው ግጭት ጀምሮ ተገድለዋል ።
 
ምንም እንኳን ለ6 ዓመታት የዘለቀው የአገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት በየካቲት ወር በተደረገ ስምምነት ቢያበቃም በተለያዩ ጊዜያት በማህበረሰቦች መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች 800 ያህል ሰዎች መሞታቸውን ባለስልጣናቱ አክለው ገልጸዋል።
 
ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ
 
#FBC
 
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.