Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያሰባሰቡትን ድጋፍ ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን በተለያዩ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሁለተኛ ጊዜ ያዋጡትን 23 ሺህ 655 የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረከቡ፡፡
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ ÷ በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገር ቤት እየተደረገ ያለውን የሕልውና ዘመቻ ጨምሮ ለሕዳሴው ግድብና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውሉ ተከታታይ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።
በተጨማሪም ዜጎች መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኝነት የላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂ በበኩላቸው ÷ በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላበረከቱት ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.