Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ አዳዲስ ገደቦች ወጡ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመራቸውን ተከትሎ አዳዲስ ገደቦችን ይፋ አደረጉ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ገደቦቹን ይፋ ያደረጉት በሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን ካለፈ ከአንድ ቀን በኋላ ነው፡፡
በዚህም ከቀብር ሥነ ሥርዓት እና ሌሎች ልዩ ልዩ ስብሰባዎች በስተቀር ሌሎች ስብሰባዎች ተከልክለዋል፡፡
ምሽት ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ የተጣለ ሲሆን ሁሉም ሱቆች ፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ የሙዚቃ ድግስና መሰል ዝግጅቶች፣ ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሁም ኮንፈረንሶች የሚዘጋጁባቸው ስፍራዎችም ዝግ ይሆናሉ፡፡
በተጨማሪም የአልኮል ሽያጭ የተከለከለ ሲሆን ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ ሲሆን÷ ይህን ማድረግ ያልቻለ ግለሰብ የገንዘብ ቅጣት ወይም እስራት ይጠብቀዋልም ነው የተባለው፡፡
በደቡብ አፍሪካ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑንም የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
አንዳንድ ሆስፒታሎች እና የህክምና ማዕከላትም ከፍተኛ የታማሚዎች ቁጥር በማስተናገዳቸው ሳቢያ ጫና እየተፈጠረባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.