Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካ በኳዝሉ-ናታል ግዛት ብቻ ባለፈው ሣምንት በተከሰተ ሁከት በ40ሺህ የንግድ ተቋማት ላይ ጥቃት ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ አፍሪካ በኳዝሉ-ናታል ግዛት ብቻ ባለፈው ሣምንት በተከሰተ ሁከት 40 ሺህ የንግድ ተቋማት ላይ ጥቃት መድረሱ ተገለጸ፡፡
በደቡብ አፍሪካ በተከሰተው ሁከት ከ70 በላይ ሰዎች ህይዎት ማለፉ የሚታወስ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪ የንግድ ተቋማት ላይ ዝርፊያ እና ውድመት ተፈጽሟል፡፡
የሃገሪቱ ባለሥልጣናት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ከታሰሩ በኋላ የጀመረው የዘረፋ እና የኃይል አመፅ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ኪሣራ ማስከተሉን እየገመገሙ ነው፡፡
በዚሁ መሠረት በኳዝሉ-ናታል ግዛት ብቻ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ ኪሣራ መድረሱ ተገልጿል፡፡
አንድ ሚኒስትር እንደተናገሩት፥ ብጥብጡና ዘረፋው በኳዝሉ-ናታል ግዛት ብቻ በ40 ሺህ የንግድ ድርጅቶ ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡
የደቡብ አፍሪካ የንብረት ባለቤቶች ማህበር የቀረበውን መረጃ በመጥቀስ ኩምቡድዞ ንፅሃቨኽኒ ግዛት ከ200 በላይ የገበያ ማዕከሎች መዘረፋቸውን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም በደርባን ብቻ ከ1ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ የሚገመት ንብረት እንደጠፋ ተናግረዋል፡፡
በተከሰተው ሁከት 90 ፋርማሲዎች የወደሙ ሲሆን፥ 1ሺህ 400 የሚጠጉ የገንዘብ ማውጫ ማሽኖች ኢላማ ሲደረጉ፥ ይህም በጆሃንስበርግ የደረሰውን ጉዳት አያካትትም፡፡
ለተፈጸመው ዝርፊያ ድህነትና ሥራ አጥነት ምክንያት መሆናቸው ተነግሯል፡፡
ሚኒስትሩ እንዳሉት፥ 150 ሺህ ስራዎች በአመጹ አደጋ የተደቀነባቸው ሲሆን፥ የባለሥልጣናቱ ግምገማ እንደቀጠለ ነው፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.