Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካ ከተከሰተው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ብሪታንያ የጉዞ እገዳ አስተላለፈች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሪታንያ በደቡብ አፍሪካ ከተከሰተው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ወደ ሃገሪቱ የሚደረጉ በረራዎችን ማገዷን አስታወቀች፡፡

አዲሱ ቫይረስ የተለየው ከደቡብ አፍሪካ ከተመለሱ ተጓዦች ሲሆን በለንደን እና በሰሜናዊ ምዕራብ እንግሊዝ ነው መከሰቱ ተረጋግጧል፡፡

ብሪታንያ ባለፉት 15 ቀናት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርተው የነበሩ ዜጎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ አዛለች፡፡

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ማት ሃንኩክከደቡብ አፍሪካ ጋር የተያያዘው አዲሱ ቫይረስ አሳሳቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህ በደቡብ አፍሪካ ተከሰተ የተባለው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በብሪታንያ ከተከሰተው ቫይረስ ጋር እንደሚመሳሰል ተገልጿል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተመራማሪዎች የቫይረሱ ሁኔታ በጥናት ላይ እንዳለ ቢገልጹም በፍጥነት እንደሚዛመት  ነው የተናገሩት፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.