Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ህብረተሰቡ ለአስቸካይ ጊዜ አዋጁ አተገባበር ያሳየው ተነሻሽነት ስኬታማ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኘው ህዝብ ለአስቸካይ ጊዜ አዋጁ አተገባበር ያሳየው ተነሻሽነት ስኬታማ መሆኑን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ገልጸዋል ።

ሀላፊዋ የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ እስካሁን ያለውን አፈጻጸም ግምገማ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኘው ህዝብ ለአስቸካይ ጊዜ አዋጁ አተገባበር ያሳየው ተነሻሽነት ስኬታማ ነው ብለዋል።

በክልሉ የመገናኛ መሳሪያዎች ምዝገባ በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን የገለጹት ኃላፊዋ በተለይ የጦር ሜዳ መነጽር፣ ኮምፓስ፣ ጂፒኤስ፣የመገናኛ ሬዲዮ፣ የሳተላይት ስልክ፣ ቪሳት እና ቢጋሮችን ማስመዝገብ እንደሚገባ አብራርተዋል።

ህብረተሰቡ እነዚህን የመገናኛ መሳሪያዎች በአቅራቢያው በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲያስመዘግብ ሀላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል።

እንደ ኃላፊዋ ገለጻ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም ከፍተኛ ካደረገው ጉዳይ አንዱ በክልሉ በሁሉም መዋቅሮች ያለው ህዝባዊ አደረጃጀት ተጠቃሽ ነው።

ስልጠና ወስዶ ወደ ተግባር የገባው ህዝባዊ ሰራዊት አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ መሆኑንም ኃላፊዋ አስረድተዋል።

ህብረተሰቡ የትኛውንም የወንጀል ድርጊት እና የወንጀል ተባባሪነት እንቅስቃሴ መጠቆም እንዲችል 9894 ነጻ የስልክ መስመር መዘጋጀቱንም ኃላፊዋ መግለጻቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.