Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ለአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አንደኛ ሽናሌ እንደገለጹት÷የደን፣ የፍራፍሬና የቡና ችግኞችን በሰባት የችግኝ ጣቢያዎች ላይ ቀጥተኛ ድጋፍ በማድረግ 450 ሚሊየን ችግኝ ለተከላ በማድረስ 61 በመቶ አፈጻጸም ተመዝግቧል፡፡
በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የፍራፍሬ ችግኝ ለሴቶችና ለወጣቶች ስራ ከመፍጠር ባሻገር የገቢ ማስገኛ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
 
አርሶ አደሮች የራሳቸውን የምግብ ዋስትና እንዲያረጋግጡ ለማስቻል በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 30 የፍራፍሬ ችግኞችን በነፍስ ወከፍ እንዲተክሉ በማድረግ ለሶስት ዓመታት 100 ችግኞች በአርሶ አደር ማሳዎችና ጓሮዎች እንዲተከሉ ለማስቻል በእቅድ ተይዞ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
እንደ ግብርና ቢሮ ብቻ በበልግ ከሚተከለው 300 ሚሊየን ችግኝ ባሻገር 430 ሚሊየን ችግኞችን በክረምት ለመትከል ዝግጅት ተጠናቋል ማለታቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.