Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል በተያዘው ዓመት ለህዳሴ ግድብ 200 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል በተያዘው ዓመት ለህዳሴ ግድብ ግንባታ 200 ሚሊየን ብር ከህብረተሰቡ ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በደቡብ ክልል በህብረተሰቡ ሰፊ ተሳትፎ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ነው የተገለጸው፡፡

በዚህ ዓመትም የክልሉን አጠቃላይ ድጋፍ ወደ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ለማሳደግ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

የክልሉ ህብረተሰብ የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት እስከሚበቃ ድረስም ድጋፉን አጠናክሮ ለመቀጠል ቃል የገባ ሲሆን ÷በዚህ ዓመት እስከ 200 ሚሊየን ብር የሚደርስ ድጋፍ ለማሰባሰብ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት አስታውቋል።

ማስተባበሪያ ምክር ቤቱ የአፈጻጸም ግምገማውን በዲላ ከተማ እያካሄደ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.