Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል በ157 ከተሞች የሴቶች የውይይት መድረኮች ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በሚገኙ 157 ከተሞች የሴቶች የውይይት መድረኮች ተካሄዱ፡፡

የደቡብ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ፥ በክልሉ ከተሞች የተዘጋጁት የውይይት መድረኮች ዋና ዓላማ የብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ የመከረባቸውን ጉዳዮች ለኅብረተሰቡ ግልጽ ማድረግ ነው ብለዋል።

በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ባለው መድረክ የተገኙት ዋና አፈ ጉባኤዋ፥ በብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የተነሱትን የውሳኔ ሃሳቦች ያብራሩ ሲሆን፥ ኅብረተሰቡ ቀደም ብሎ ሲያነሳቸው የነበራቸውን ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ የዕቅድ አካል ሆነው ወደ ተግባር መግባት የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመሩንም አንስተዋል።

በሀገር አቀፍም ሆነ በክልል ደረጃ የህዝብ ውይይቶች መካሄዳቸውን የተናገሩት ዋና አፈ ጉባኤዋ፥ ከፓርቲው የጉባዔ ውሳኔዎች አንጻር ሴቶች ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው አቋም በመወሰዱ በዚህ መድረክ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ተግባር ለመግባት የሚያስችል አቅጣጫ ይቀመጣል ብለዋል፡፡

የውይይት መድረኮቹ ሴቶች የውሳኔ ሃሳቡን ተግባራዊ ለማድረግ ያላቸውን ሚና እና ከመንግስት ጋር ሆነው በሀገሪቱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ያላቸውን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያመላክታልም ብለዋል።

በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ባለው መድረክ የከተማዋ ከንቲባ አቶ አብርሐም መጫ፥ ከልማት እና ከመልካም አስተዳደር አንጻር የተከናወኑ ተግባራት ላይ ገለጻ ማድረጋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.