Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል በ2012/13 የምርት ዘመን በበልግ አዝመራ ከ84 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ መሰብሰብ እንደተቻለ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በ2012/13 የምርት ዘመን በበልግ አዝመራ ከ84 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ እንደተቻለ ተገለጸ፡፡
በክልሉ በወቅታዊ የግብርና ስራዎች አፈጻጸም እና ቀጣይ አቅዳጫዎች ላይ የምክክር መድረክ በሀላባ እየተካሄደ ነው።
በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት በ2012/13 የምርት ዘመን በበልግ እርሻ በአዝዕርት በስራስር እና አትክልት ሰብሎች 1 ሚሊየን 135 ሺህ ሄክታር መሬት ማልማት የተቻለ ሲሆን 84 ሚሊየን 318 ሺ 764 ኩንታል ምርት መሰብሰብ ተችሏል፡፡
ከ2011/12 የምርት ዘመን ጋር ሲነጻጸር በ13 በመቶ የምርት ጭማሪ መኖሩን አቶ አንተነህ አብራርተዋል፡፡
በግብርና ስራዎች ላይ የተስተዋሉ ችግሮችን በመፈተሽ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራም አብራርተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.