Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ460 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም ሰብሎች እየለማ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ከ460 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም ሰብሎች እየለማ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ እየለማ ያለውን የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡
በዚህ እንደገለጹት በክልሉ በተያዘው የምርት ዘመን ከ460 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም ሰብሎች እየለማ ነው፡፡
እንደ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ በክልሉ በኩታ ገጠም ሰብሎች እየለማ ካለው መሬት ውስጥ ከ160 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ሰብል የተሸፈነ ሲሆን 143 ሺህ ሄክታሩ ደግሞ በጤፍ፣ በባቄላ፣ በሆርቲካልቸር እና መሰል ሰብሎች በዘር መሸፈኑን አስረድተዋል፡፡
በክልሉ በመኸር እርሻ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል፡፡
ይህም ካለፈው አመት አፈጻጸም አንጻር በ95 ሺህ ሄክታር መሬት ብልጫ ማሳየቱን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.