Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ5 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ-19 የመከላከያ ክትባትተከትበዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ከ5 ሚሊየን በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ-19 የመከላከያ ክትባት እንደተከተቡ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ እየተሰጠ ባለው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ምክንያት በበሽታ የሚያዙ እና የሚሞቱ የህብረተሰብ ክፍሎች በከፍተኛ ቁጥር መቀነሱን የቢሮው ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ ተናግረዋል።

ከክትባቱ ጋር የሚነሱ አሉባልታዎች ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከጋዜጠኞች እና ከክልሉ ከፍተኛ አመራርሮች ጋር ጥልቅ ውይይት መደረጉንም አቶ እንደሻው ገልፀዋል።

በዚህም በደቡብ ክልል የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ይወሰዳሉ ተብሎ ከተለዩ ከ7 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች 5 ሚሊየን 420 ሺህ 594 ያህሉ ክትባት የወሰዱ ሲሆን ÷ከነዚህ ውስጥ 3 ሚሊየን 454 ሺህ 760 ያህሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባታቸውን ወስደው ያጠናቀቁ ናቸው ተብሏል።

የሦስተኛው ክትባት ዘመቻው በክልሉ በሁሉም የመንግሥት ጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ መነሃሪያዎች እንዲሁም በተመረጡ የአርብቶ አደር አካባቢዎች የቤት ለቤት እየተሰጠ እንደሆነ ተናግረው ዕድሜያቸው 12 አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን እንዲወስዱ ማሳሰባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.