Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ94 ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት ክልል አቀፍ የውይይት መድረክ በተለያዩ ከተሞች እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በተቀመጡ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ክልል አቀፍ የወጣቶች መድረክ በ157 ከተሞች ወጣቶችን ያሳተፈ ውይይት በመካሔድ ላይ ይገኛል፡፡
 
በብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ዋና ጽህፈት ቤት የአደረጃጀች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስመኘው አድነው በሆሳዕና ከተማ በተጀመረው መድረክ እንደተናገሩት፥ በብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት ለማሳደግ የሚያስችሉ ውሳኔዎች ተላልፈዋል።
 
በፓርቲው የተቀመጡ አቅጣጫዎችን እና ውሳኔዎችን በመፈጸም ሂደት ወጣቱ ግንባር ቀደም ተዋናይ ነው ያሉት ኃላፊው፥በየደረጃው በሚካሔዱ የውይይት መድረኮች ወጣቶች ገንቢ አስተያየት በማቅረብ በሀገሪቱ እየተካሔደ ያለውን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
 
በጉባኤው በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ የሚያደርጉ ውሳኔዎች መተላለፋቸውንም አብራርተዋል።
 
በመድረኩ ከልማት እና ከመልካም አስተዳደር አንጻር የተከናወኑ ተግባራት በሆሳዕና ከተማ ከንቲባ በአቶ አብረሐም መጫ ገለጻ የተደረገ ሲሆን፥ በቀጣይ የውይይቱ ተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.