Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል የህብረተሰብ አቀፍ የተፋሰስ የልማት ስራ በኮንሶ ዞን በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የህብረተሰብ አቀፍ የተፋሰስ የልማት ስራ በኮንሶ ዞን በይፋ ተጀመረ፡፡
ከተፈጥሮ አደጋ እራስን ለመታደግ ተፈጥሮን መንከባከብና ማልማት ያስፈልጋል ሲሉ በክልል አቀፍ ይፋዊ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ እርስቱ ይርዳ ተናግረዋል፡፡
 
የኮንሶ ህዝብ በባህላዊ የእርከን ስራ ተሞክሮውን ለሌሎች ማጋራትና ይሄንንም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለጹ ሲሆን÷ ዞኑ በተፈጥሮ አደጋ ዋጋ እየከፈለ ስለሆነ በልዩ ትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
 
የመሬት መሸርሸርና ናዳን የመከላከል ስራ የህልውና ጉዳይ አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ሲሉም አክለዋል፡፡
የግብርና ልማት ስራው በመንግስት ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ገልፀው፥ በየአመቱ በቢሊየን የሚቆጠር ችግኝ እንደሚተከል ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል፡፡
የተቀናጀ የልማት ስራ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ናቸው፡፡
የተፋሰስ የልማት ስራን በትኩረት በመስራት በአፈር መሸርሸር ምክንያት ጉዳት የሚደርስባቸውን አርብቶና አርሶ አደር አካባቢዎች መታደግ እንደሚቻልም ነው የተናገሩት።
 
ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ከ2 ሺህ 376 በላይ ተፋሰሶች መለየታቸውን ከክልሉ ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
 
በዚህ የተፋሰስ ልማት ስራ ከ3 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
 
በብርሃኑ በጋሻው
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.