Fana: At a Speed of Life!

በደብረማርቆስና ሻሸመኔ ከተሞች ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረማርቆስና ሻሸመኔ ከተሞች ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጥራት ያለውና አስተማማኝ ለማድረግ የዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት እየተከናወነ መሆኑን የስድስቱ ከተሞች የማሻሻያና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ምንተስኖት ተስፋዬ ገለጹ፡፡
የፕሮጀክቱ የስራ ወሰን በደብረማርቆስ ከተማ 95 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር፣ 55 ነጥብ 25 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ማሻሻያ ግንባታና ነባር መስመሮችን የማንሳት፣ የ15 ነባር የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች ማሻሻል፣ የ21 አዲስ የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች እና 3 ሺህ 857 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ ይከናወናል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በሻሸመኔ ከተማ 99 ነጥብ 73 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣ 86 ነጥብ 2 ኪ.ሜ የዝቀተኛ መስመር ማሻሻያ ግንባታና ነባር መስመሮችን የማንሳት፣ የ17 ነባር የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች ማሻሻል፣ የ27 አዲስ የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮችንና 5 ሺህ 372 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ እንደሚከናወን ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል፡፡
ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ ከአለም ባንክ በተገኘ 9 ሚሊየን 562 ሺህ 906 ነጥብ 54 ዶላር ብድር እና 67 ሚሊየን 791 ሺህ 61 ብር ከ38 ሳንቲም ተመድቦ በቻይና ተቋራጭ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት መሰረታዊ የዲስትሪቢዩሽን ዕቃዎች የዲዛይንና የቴክኒካል ስፔሲፊኬሽን የማጽደቅ ስራ መጠናቀቁን የገለፁት አቶ ምንተስኖት፥ መቶ በመቶ የመካከለኛ እና የዝቅተኛ መስመር ኤሌክትሪክ ኮንዳክተሮች ወደ ሃገር ገብተው የጥራት ፍተሻ መደረጉንም አንስተዋል፡፡
በአጠቃላይ ለስራው ከሚያስፈልገው 9 ሺህ 229 የመካከለኛና የዝቅተኛ መስመር ምሰሶዎች ውስጥ 4 ሺህ 797 ተመርተውና የጥራት ፍተሻቸውን አልፈው ወደ ሻሸመኔ እና ደብረ ማርቆስ ከተሞች መጓጓዛቸውን የገለፁት ስራ አስኪያጁ÷ የመካከለኛና የዝቅተኛ መስመር የምሰሶ ማቆም ስራው 45 በመቶ ስራ እንዲከናወን ተደርጓል ብለዋል፡፡
የስድስቱ ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን መስመር መልሶ ግንባታና አቅም የማሳደግ ፕሮጀክት እንዲፋጠን በማድረግ በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ 95 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝ መናገራቸውን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በስድስት ከተሞች ማለትም በጎንደር፣ በአዲግራት፣ በሀረር ፣ በሻሸመኔ፣ በደብረማርቆስና በወላይታ ሶዶ በ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የኤሌክትሪክ መስመሮች የማሻሻልና መልሶ ለመገንባት አቅዶ ስራ መጀመሩ ይወቃል፡፡
ፕሮጀክቱ ከአዲግራት ከተማ በስተቀር በሁሉም ከተሞች በዕቅዱ መሰረት እየተከናወነ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.