Fana: At a Speed of Life!

በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የልደት በዓል በሰላም ተጠናቋል- የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስና የቅዱስ ላሊበላ የልደት በዓል ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ፣ ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና ምዕምናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።

የልደትን በዓል መሰላም መጠናቀቅ አስመልክቶ በላሊበላ መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የልደት በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

በዚህ ዓመት የልደት በዓል በላሊበላ በልዩ ሁኔታ እንዲከበር ጥሪ ተለላልፎ እንደነበርም አስታውሰዋል።

በተደረገው ጥሪ መሠረት በታላቅ ድምቀት መከበሩንም አስታውቀዋል። አካባቢው በአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ቡድን ተወርሮ የነበረ ቢሆንም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት መከበሩንም ገልፀዋል።

በዓሉ በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች በፀጥታ ኃይሎች ጥመረት፣ በወጣቶች እና በሰላም ወዳዱ ሕዝብ የጋራ ትብብር በሰላም መጠናቀቁን ነው የተናገሩት። የፀጥታ ችግር እንዳይኖር ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ግዛቸው ልክ እንደ ላሊበላ ሁሉ ጥምቀትን በጎንደር ብዙ ሕዝብ በተገኘበት በታላቅ ድምቀት እናከብራለንም ብለዋል። ክልሉ ሰላማዊ መሆኑ ታውቆ ቀጣይ በሚኖሩት በዓላት ሕዝቡ በስፋት እንዲታደምም ጥሪ አቅርበዋል።

የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች ፣ የክልሉ ሕዝብና የፀጥታ ተቋማት የልደት በዓል በላሊበላ በሰላም እንዲከበር እንዳደረጉ ሁሉ ቀጣይ የሚከበሩ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ የተለመደውን ኃላፊነት እንድትወጡ ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.