Fana: At a Speed of Life!

በደብረ ብርሀን ከተማ በ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የተገነባው ቦርት ማልት ብቅል ፋብሪካ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደብረ ብርሀን ከተማ በ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የተገነባው ቦርት ማልት ብቅል ፋብሪካ ዛሬ  ብቅል ማምረት ጀመረ፡፡

በፈረንሳይ ባለሀብቶች የተገነባው ፋብሪካው በዓመት 60 ሺህ ቶን ብቅል የማምረት አቅም አለው ተብሏል፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ በደብረ ብርሀን ከተማ ተገኝተው ስራ አስጀምረዋል፡፡

ፋብሪካው በኢትዮጵያ ለሚገኙ 14 የቢራ ፋብሪካዎች የብቅል ፍጆታዎችን እንደሚሸፍን ይጠበቃል፡፡

ቦርት ማልት ፋብሪካ በዓመት ለሚያመርተው ብቅል ከ40 ሺህ አርሶ አደሮች የገብስ ምርት እንደሚቀበልም ተገልጿል፡፡

ፋብሪካው አሉብኝ ያላቸውን የመሰረት ልማት ጥያቄዎች የክልሉ መንግስት እንደሚፈታ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በስነስርኣቱ ላይ አሳውቀዋል፡፡

ቦርት ማልት ብቅል ፋብሪካ በደብር ብርሀን ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ስራ የጀመረ ሁለተኛው ፋብሪካ ሆኗል፡፡

 

በአላዩ ገረመው

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.