Fana: At a Speed of Life!

በደብረ ብርሃን ከተማ ለተደራጁ የመኖሪያ ቤት ኅብረት ስራ ማህበራት 30 በመቶ በዝግ አካውንት የሚቆጠብ ብር መጠን ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ ለተደራጁ የመኖሪያ ቤት ኅብረት ስራ ማህበራት 30 በመቶ በዝግ አካውንት የሚቆጠብ ብር መጠን መወሰኑን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ እንደገለፁት÷ በከተማው በመኖሪያ ቤት ኅብረት ስራ ማኅበራት ለተደራጁ ነዋሪዎች የከተማው ህንፃ ሹም ጽህፈት ቤት የሚሰሩትን ቤቶች ንድፍና የህንፃ ግምታቸውን ጥናት አሳውቋል፡፡
በጥናቱ ግምቱ ከፍ ያለ ቢሆንም የኅብረተሰቡን የመቆጠብ ባህልና የአቅም ውስንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ውሳኔው ተላልፏል ነው የተባለው፡፡
በተወሰነው መሰረትም ለባለ 1 መኝታ ቤት 35 ሺህ ብር፣ ለባለ 2 መኝታ ቤት 38 ሺህ ብር እና ለባለ 3 መኝታ ቤት 40 ሺህ ብር እንዲቆጥቡ የከተማ አስተዳደሩ ወስኗል፡፡
ከንቲባው አክለውም የመኖሪያ ቤት ኅብረት ስራ ማኅበራት አባላት የቁጠባ ውሳኔው ይህ መሆኑን አውቀው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት ተጠቀሰውን ብር ለመቆጠብ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ይህ የአሁኑ ግምት ከካሳ ግምቱ ጋር የማይገኛኝ መሆኑን የገለፁት ከንቲባው የካሳ ግምቱም ለሁሉም ማኅበራት አንድ አይነት እንደማይሆን ጠቁመዋል፡፡
የካሳ ግምቱ እንደቦታው ሁኔታ የተወሰነ ልዩነት እንደሚኖረውና በተቻለ መጠን ግምቱ ተመጣጣኝ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ ጥረት እንደሚያደርግ መናገራቸውን ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.