Fana: At a Speed of Life!

በዲላ ከተማ የመስጂዶች ማህበር በደብረ ብርሀን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን ዲላ ከተማ የመስጂዶች ማህበር በደብረ ብርሀን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ በመሆኑ ነው ይህንን ድጋፍ ያደረግነው ሲሉ÷ የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጀማል አብደላ ገልጸዋል፡፡
የተደረገው ድጋፍ የ 2 ሚሊየን 639 ሺህ ብር ግምት ያለው ሲሆን÷ ምግብ ነክ፣ አልባሳትና የማብሰያ ቁሳቁስ ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ በኋላ ወገኖቻችን እየተቸገሩ ዝም አንልም ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወ/አማኑኤል÷ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በአይናለም ስለሺ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.