Fana: At a Speed of Life!

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተከስቶ የነበረው አስከፊው የኢቦላ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ከሁለት ዓመት በፊት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል ።

በርካታ የታጠቁ ቡድኖች በሚንቀሳቀሱበት ሰሜናዊ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል በፈረንጆቹ ከሚያዝያ 27 ወዲህ በበሽታው የተያዘ አዲስ ሰው አለመመዝገቡም ነው የተነገረው።

ወረርሽኙን በቁጥጥር ስር ለማዋል የኢቦላ ክትባት ዘመቻ መስፋፋቱን ቁልፍ ሚና መጫወቱ ተገልጿል።

በአገሪቱ የኢቦላ ወረርሽኝ ከተከሰተ በፈረንጆቹ 2018 ጀምሮ 2ሺህ 280 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል ፡፡

ከዚያም ባለፈ በምዕራብ አፍሪካ ይህ አስከፊ ወረርሽኝ በአውሮፓውያኑ በ 2014 እና በ 2016 መካከል ከ 11 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸው ይነገራል ፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት የአገሪቷ 11 ኛ ጊዜ ወረርሽኝ የተከሰተባት ማባነዳካ ውስጥ ያለው ሁኔታ በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቁሞ÷ ነገር ግን ኢቦላ ቫይረስ በእንስሳት ውስጥ ሊኖር ስለሚችል አዲስ የኢቦላ ወረርሽኝሊከሰት እንደሚችል ተናግሯል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.