Fana: At a Speed of Life!

በዳርፉር የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ኃይል ተልዕኮውን አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪካ ህብረት በጥምረት በሱዳን ዳርፉር ያሰማሩት ሰላም አስከባሪ ኃይል ተልዕኮ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

የሰላም አስከባሪ ኃይሉ /ዩናሚድ/ ትናንት ባወጣው መግለጫ የሱዳን መንግስት ጸጥታ እና ደህንነት ለማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወስዳል ብሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት 15 አባላት የያዘው የጸጥታው ምክር ቤት ሰላም አስከባሪ ኃይሉ ተልዕኮው እንዲያበቃ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ይህን ተከትሎም ደረጃ በደረጃ እንደሚወጡ የተገለጸ ሲሆን በሰኔ ወር ጠቅለው እንደሚወጡ ተገልጿል፡፡

በዳርፉር የተሰማራው የተመድ ሰላም አስከባሪ ሃይል (ዩናሚድ) ከ2007 ጀምሮ ለ13 ዓመታት በዳርፉር ተልዕኮ ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

በሌላ በኩል ሰላም አስከባሪ ሃይሉ በነበረባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች የዩናሚድ ተልዕኮ ማብቃትን ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸው ተነግሯል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.