Fana: At a Speed of Life!

በዳንጉር ወረዳ በህወሓት ተላላኪዎችና ሽፍቶች ጫና ከአካባቢያቸው ሸሽተው የነበሩ 100 የጉምዝ ማህበረሰብ አባላት ወደ ወረዳ ማዕከል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ህወሓት ያሠማራቸው ተላላኪዎችና ሽፍቶች የሚፈጥሩትን ጫና ሸሽተው የነበሩ 100 የጉምዝ ማህበረሰብ አባላት በዛሬው ዕለት ወደ ወረዳ ማዕከል እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
በዞኑ የሚንቀሳቀሱ የህወሓት ተላላኪ ኃይሎች የጉሙዝ ማህበረሰብን ከወንድም ህዝብ ጋር የነበረውን አብሮነት በማሻከር ርዕስ በርዕስ እንዲጠራጠሩ በማድረግ ያልተገባ ጫና በመፍጠር ቀበሌያቸውን ለቀው ለበርካታ ወራት ጫካ ሸሽተው መቆየታቸው ተገልጿል፡፡
በጥፋት ኃይሎች ተፅዕኖ በጫካ ውስጥ የነበሩ የአይፓፖ፣ አዛርቲ ክትሊ፣ ደቡህ ኮክል እና ጊፂ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 100 የጉምዝ ማህብረሰብ አባላት በወረዳ ማዕከል እንዲጠለሉ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡
የዳንጉር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ብርሃኑ ክንፉ እንደገለፁት፥ በአሸባሪው ህወሓት ተላላኪ ግፍና በደል ለተጎዱት የስነ ልቦና ምክር በመስጠት መረጋጋትን ለማምጣት የጋራ ጥረት ይጠይቃል፤ ጠላትን መደበቂያ ማሳጣት ይኖረብል ብለዋል፡፡
ወደ ማዕከል የተመለሱ ዜጎች በበለኩላቸው፥ የጥፋት ኃይሉ ባደረሰባቸው ተፅዕኖ ለመሸሽ መገደዳቸውና በጫካ ቆይታቸው ለረሃብና ለበሽታ ማዳረጋቸው ገልፀዋል፡፡
አሁን መንግስት ባደረገላቸው ጥሪ ከጨለማ ወጥተው ብርሃን ለማየት በመብቃታቸውና ከወንድም ህዝብ ጋር ለመገናኘት በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሌሎች ወገኖቻቸው ከጥፋት ቡድኑ ጫና ራሳቸውን በማላቀቅ ወደ ወረዳ ማዕከል እንዲመጡ ተመላሽ የጉሙዝ ማህበረሰብ አባላቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የዳንጉር ወረዳ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሻንበል ደምስ ዳኛው÷ የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስቱና የፖለቲካ አመራሩ በጋራ በሠሩት ስራ እነዚህ ንፁሀን የህብረተሠብ ክፍሎች ከአሸባሪው ተላላኪዎች ነጻ ወጥተው ወደ ወረዳ ማዕከል እንዲመጡ ተደርጓል ብለዋል፡፡
የጉሙዝ ብሔረሰብ ምክር ቤት አፈ ጉባኤን ጨምሮ የዞንና የወረዳ አመራሮች አቀባበል ማድረጋቸውን ከቡኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.