Fana: At a Speed of Life!

በዳውሮ ዞን የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል  ክትባት መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም   የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል  ክትባት መሰጠት ተጀመረ ፡፡

ከዚህ ባለፈም በተርጫ ከተማ እና በተርጫ ዙሪያ  ወረዳ በቦጲ አራ እና በሜላ ቀበሌዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ  ስራ መሰራቱም ታውቋል።

ክትባቱ በተርጫ ከተማ በአራቱ ቀበሌዎች ተደራሽ ይደረጋሉ ተብሎ ከሚታሰበው 25 ሺህ 250 ሰዎች ውስጥ በሁለቱ ቀናት 9 ሺህ 595 ሰዎች  ክትባቱን ወስደዋል ነው የተባለው፡፡

እንዲሁም  በተርጫ ዙሪያ ወረዳ ቦጲ አራ ቀበሌ 3 ሺህ 210 ሰዎች ይከተባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን÷ በሁለቱ ቀናት ውስጥ 833 ሰዎች መከተባቸውም ተገልጿል።

በአካባቢዎቹ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች የማይተገበሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወረርሽኙ እንዳይባባስ ባለድርሻ አካላት የመከላከሉን ስራ በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል መረባረብ  እንደሚገባቸው መገለፁን ከዳውሮ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.