Fana: At a Speed of Life!

በዳውሮ ዞን የድምፅ ቆጠራ በተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት በየምረጫ ጣቢያው እየተለጠፈ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በዳውሮ ዞን የድምፅ ቆጠራ በተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት እየተለጠፈ ነው ይገኛል።
ትላንት መስከረም 20/2014 በዳውሮ ዞን በሎማ ቦሳ የምርጫ ክልል 6ኛ ሀገራዊና በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች በተካሄደው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔ የድምፅ ቆጠራ በተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት እየተለጠፈ ይገኛል።
ያለ ምንም የፀጥታ ችግር ምርጫው መጠናቀቁን የገለፁት አስተያየት ሰጭዎች÷ ጊዜያዊ ውጤቱ በፍጥነት በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፉም እንዳስደሰታቸው መናገራቸዉን የዘገበዉ የዳዉሮ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.