Fana: At a Speed of Life!

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኩፍኝ ወረርሽኝ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኩፍኝ ወረርሽኝ እስካሁን ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የዓለም ጤና ድርጅት የበሽታው ስርጭት እጅግ ፈጣን መሆኑንም አስታውቋል።

ካለፈው የፈረንጆቹ አመት መጀመሪያ አንስቶ 310 ሺህ የሚጠጉ የበሽታው ተጠቂዎች በሃገሪቱ ተገኝተዋልም ነው ያለው።

ወረርሽኙ ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ በሃገሪቱ ከተሰከተ በኋላ በ26 ክልሎች የኩፍኝ በሽታ መታየቱ ተነግሯል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በመላ ሃገሪቱ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ከ18 ሚሊየን በላይ ህጻናት ክትባት ማግኘታቸው ተገልጿል።

ደካማ መሰረተ ልማት፣ በጤና ማዕከሎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እና የመደበኛ ጤና አጠባበቅ እጥረት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ለሚደረገው ጥረት እንቅፋት መሆናቸውንም ድርጅቱ ገልጿል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ማሺዲሶ ሞኤቲ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.