Fana: At a Speed of Life!

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዳግም የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ሊከሰት ይችላል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዳግም የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ይከሰታል መባሉን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለስደት ተዳርገዋል፡፡

የሃገሪቱ መንግስት በጎማ ከተማ ዳግም የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ሊከሰት እንደሚችልና የከተማዋ ነዋሪዎችም ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡

እንደሃገሪቱ መንግስት ማስጠንቀቂያ ከሆነም የኒያራጎንጎ ተራራ እሳተ ገሞራ በድንገት ሊፈነዳ ይችላል፡፡

ከጎማ ከተማ በ10 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ተራራ ከአራት ቀናት በፊት በተከሰተው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ 32 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱ በርካቶች አደጋውን ሸሽተው ከከተማዋ ቢወጡም አሁን ወደ መኖሪያቸው እየተመለሱ ባለበት ወቅት ነው የአሁኑ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.