Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ1 ቢሊየን 75 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘጠኝ ወራት ውስጥ 1 ቢሊየን 267 ሚሊየን 936 ሺህ 139 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 1 ቢሊየን 75 ሚሊየን 575ሺህ 415 ብር መሰብሰቡን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ በዘጠኝ ወራት ውስጥ መንግስት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ግብር ከፋዩ ላይ የደረሰውን የኢኮኖሚ ጫና ለመታደየተደረገውን ከ120 ሚሊየን ብር በላይ ድጎማ ሳያካትት 1 ቢሊየን 75 ሚሊየን 575ሺህ 415 ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡
ይህም የዕቅዱን 84 ነጥብ 8 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው የገለፁት ፡፡
ይህ አፈፃፀም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ 116 ሚሊየን 766 ሺህ 722 ብር ብልጫ እንዳለው መገለፁን ከድሬደዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመጋቢት ወርም 137 ሚሊየን 402 ሺህ 956 ብር ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ በጀት አመት ወር ጋር ሲነፃፀር የ27 ሚሊየን 380 ሺህ 69 ብር ብልጫ እንዳላው ተገልጿል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ እንደገለፁት፤ የወሩን እቅድ 97 ነጥብ 5 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.