Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ አስተዳደር “ምክንያት አልሆንም” የኮቪድ19 ወረርሽኝ መከላከል የንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በድሬዳዋ አስተዳደር “ምክንያት አልሆንም” የኮቪድ19 ወረርሽኝ መከላከል የንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ ተጀመረ፡፡

ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስተባባሪነት “ምክንያት አልሆንም” የኮቪድ19 የማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡

የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ በመርኃ ግብሩ በቀጣይ 15 ቀናት ብቻ ከ5 ሺህ 131 በላይ ለወረርሽኙ ተጋላጭ ናቸው ተብለው የሚታመኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በምርመራ ለመድረስ ታልሞ ወደ ትግበራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

ለዚህ ስኬት በዕለቱ የተገኙ ባለድርሻ አካላትም ሆነ የህብረተሰቡ ትብብር ለስራው ውጤታማነት ሰፊ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በበኩላቸው ኮቪድ19 በአሁኑ ሰአት በአስተዳደሩ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለዚህም በህብረተሰቡ የወጡ የጥንቃቄ መርሆዎች አለመተግበርና የህግ ጥሰቶች ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰው ስርጭቱን ለመቆጣጠር የሁሉም ርብርብና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በስነ ስርአቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ቡርማ ሳምቦ በበኩላቸው ኮቪድ19 እያሳደረ ያለውን ችግር ለመቀልበስና ቫይረሱን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን የዓለም ጤና ደርጅት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ19 ምርመራ ማድረጋቸውን ከአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.