Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ተከሰተ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው – የፌደራል ፖሊስ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ተከሰተ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
የድሬዳዋ ሲቪል አቪየሺን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሽመልስ፥ ትናንት የአውሮፕላኑን አቅጣጫና የርቀት መለኪያ፣ የኃይል መቆጣጠሪያና የመገናኛ መሳሪያ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል መጨመር ምክንያት በተከሰተ ቃጠሎና ፍንዳታ የኃይል መቆጣጠሪያ ስርዓቱ ላይ አደጋ መድረሱን ገልፀዋል፡፡
የተከሰተው አደጋ በባለሙያዎች ምርመራ ከተደረገበት በኋላ በቀጣይ ለአውሮፕላን በረራ ምቹ የሚሆንበትን መንገድ በማመቻቸትና አስፈላጊውን ጥገና በማድረግ በዛሬው ዕለት ከማለዳው 1፡00 ሰዓት ጀምሮ የአውሮፕላን በረራ እንዲካሄድ መደረጉን ተናግረዋል።

ይህንን የኤሌክትሪክ አደጋ አንዳንድ ግለሰቦች በአሸባሪው ህወሓትና ሸኔ ቡድን የፀጥታ ችግር እንደተከሰተ እና የተኩስ ልውውጥም እንደተፈጠረ አስመስለው ውዥንብር በመፍጠር ሐሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ቢያሰራጩም ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳልተከሰተና አውሮፕላን ማረፊያው የተለመደ በረራውን እያካሄደ መሆኑንም ነው የገለጹት።

የአሸባሪ ህወሓት ጁንታና የሸኔ ቡድን በነገው ዕለት በቁልቢ የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል ለማደናቀፍና በዓሉ በሰላማዊ መንገድ ተከብሮ እንዳይጠናቀቅ ሐሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጩ መሆናቸውን ፖሊስ ደርሶበታል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን በመገንዘብ ምንጩ ባልታወቀ ሐሰተኛ መረጃ ሳይደናገር እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በዓሉን በሰላማዊ መንገድ እንዲያከብር ጥሪ አስተላልፈዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.