Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የገቡ ባለሃብቶች ምርቶቻቸውን ለውጪ ገበያ ማቅረብ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የገቡ ባለሃብቶች ምርቶችን በማምረት ለውጪ ገበያ ማቅረብ ጀመሩ።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የፓርኩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ካሚል ኢብራሂም ፓርኩ ለ2 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።
ባለፉት ስድስት ወራትም 6 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት መቻሉን አቶ ካሚል ተናግረዋል።
ወደ ስራ ከገቡት ውስጥ ሀን ፕላስ የሲሚንቶ ከረጢት ማምረቻ ፣ ሀንደሪያ ጫማ ማምረቻ እና ዊሽ ፈትል ማምረቻ ኩባንያዎች ተጠቃሾች ናቸው ተብሏል።
ነገር ግን ፓርኩ ብዙ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት ቢሆንም የውሀ አቅርቦት ግን ችግር ሆኖበታል ነው የተባለው፡፡
በሁለት ምእራፍ የሚለማው ኢንዱስትሪ ፓርኩ የመጀመሪያ ምእራፉ በ150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ ሲሆን 15 ሼዶችንም የያዘ ነው።
ባለፈው አመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተመርቆ ወደ ስራ የገባው ፓርኩ 150 ሚሊየን ዶላር የግንባታ ወጪ ተደርጎበታል።
በዙፋን ካሳሁን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.