Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማካሄድ እንዲቻል በዛሬው እለት የሰላም ኮንፈረንስ አካሄደ።

በኮንፈረንሱ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ አባ ገዳዎች፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።

የሰላም ኮንፈረንሱን በይፋ ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባ አደም፥ በሰላም እጦት ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደቱ በመስተጓጎሉ ምክንያት የተማሪዎች ህይወት ከመጥፋቱ ባለፈ የአካባቢው ማህበረሰብ ተጎጂ ሆኗል ብለዋል።

በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ግጭቱን በማባባስ እጃቸው ያለበት አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የገለፁት ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቷ አሁንም እያጣራን እርምጃ እንወስዳለን ነው ያሉት።

ተማሪዎችም ቢሆኑ የመጡበትን አላማ ከማሳካት ውጪ የሌሎች አጀንዳ ማስፈፀሚያ እንዳይሆኑ አሳስበዋል።

የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎችም ተማሪዎች የመጡበትን ዓላማ ብቻ በመያዝ ትምህርታቸውን መማር አለባቸው በማለት አሳስበዋል።

በተሾመ ሀይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.