Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም የሚመራ የልዑካን ቡድን በጂቡቲ ጉብኝት አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂቡቲ ለሚገነባው የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት ግንባታ ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ አደም የተመራ የልዑካን ቡድን ጉብኝት አድርጓል፡፡

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በጂቡቲ የሚኖረውን የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ በሃገሩ ስርአት ትምህርት አማካኝነት ትምህርት ቤት በመገንባት የረጅም ጊዜ ችግሩን ለመፍታት እንዲችል ሙያዊ እገዛ ለማድረግ በመምጣቱ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ችግሩን ለጂቡቲ መንግስት አሳውቆ አራት ሄክታር መሬት መስጠቱን ተከትሎ በአሁኑ ወቅቱ በኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር ድጋፍ መታጠሩን አውስተዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው ዩኒቨርሲው ለኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት ግንባታ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት የራሱን አሻራ ለማሳረፍ ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በጂቡቲ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የተውጣጣውን ከትምህርት ቤቱ የግንባታ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር በተለይ ለዲዛይን ስራው በሚያስፈልጉ መሰረታዊ መረጃዎች ዙሪያ ተወያይቷል፡፡

የሚገነባው ትምህርት ቤት ከመዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል መሆን እንዳለበትና ደረጃ በደረጃ መገንባት እንደሚገባውም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

የአስተባባሪ ኮሚቴው አባላት ለረጅም ጊዜ ሲንከባለል የቆየውን የትምህርት ቤት ጉዳይ በዋነኛነት ራሱ በጂቡቲ የሚኖረው ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ኃላፊነቱን ወስዶ በገንዘብ፣ በሙያ፣ በጉልበትና በመሳሰሉት እንቅስቃሴ የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ከአስተባባሪ ኮሚቴው ጋር በመሆን ለትምህርት ቤት ግንባታ የሚውለውን መሬት መጎብኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.