Fana: At a Speed of Life!

በጀርመን እና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በያዝነው ሣምንት ወደ ሀገራቸው እንደሚመጡ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን እና በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን በተያዘው ሣምንት በግልና በቡድን ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ዝግጅት መጨረሳቸውን ገለጹ፡፡
በበይነ መረብ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ አካባቢዎችን በመጎብኘት አካባቢዎቹን መልሶ ለማቋቋም የአጭር እና የረጅም ጊዜ ዕቅድ መያዛቸውንም አመላክተዋል።
በውጪ ሀገር የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን በውጪ ቢኖሩም ልባቸው ግን በሀገራቸው ኢትዮጵያ እንደሆነ አስረድተው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበላቸው “ኑ ወደ ሀገራችሁ” ጥሪ የኑሮ ውጣ ውረዳቸውን ወደ ጎን ብለው ሀሳባቸውን በመሰብሰብ ወደ ሀገራቸው ለመምጣት እንዲቆርጡ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ከመጎብኘት በዘለለ በውጪ በሚኖሩበት ጊዜ ያካበቱትን እውቀት ለሀገራቸው ለማዋል እንደተዘጋጁም ነው የገለጹት።
በአሜሪካ ሲያትል በሚገኘው “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” የተሰኘ ማኅበር በኩል ሀሰተኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በመንዛት የመረጃ ጦርነት ውስጥ የገቡትን የምዕራባውያኑን መገናኛ ብዙኃን አፍ ለማዘጋት እንደሚሰራና በተላላኪው የሽብር ቡድን በግፍ ወላጆቻቸው ያጡ ህጻናትን እና የገቢ ምንጫቸው የወደመባቸውን ዜጎች በማናገር እና ዝርዝር መረጃ በመያዝ የማጋለጥ ሥራ እንደሚያከናውኑም ነው የቡድኑ አባላት የተናገሩት፡፡
ድንቅ የዓለም ቅርስ የሆኑ ቦታዎችን መጎብኘት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫናውን ለማቃለል በአፋር እና በአማራ ክልሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ማነጋገር እና የአጭር ጊዜ ድጋፍ በማድረግ በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን መንገድ መሻት ቡድኑ ዓላማው አድርጎ ይሰራልም ነው የተባለው።
ኢትዮጵያ በስርዓተ መንግስት የቀደመ ታሪክ ያላት እና ከራሷ አልፎ የአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን ወደ ሀገር ቤት የምናደርገው ጉዞ ማሳያ ነው ብለዋል።
በበላይ ተስፋዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.