Fana: At a Speed of Life!

በጀርመን የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ርቀትን በመጠበቅ መስገድ ላልቻሉ ሙስሊሞች በሯን ክፍት አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን በርሊን የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ በአንድ መስጅድ መስገድ ላልቻሉ ሙስሊሞች እንዲጠቀሙ ፈቅዳለች።

ፈቃዱ የተሰጣቸው በበርሊን በሚገኘው ዳር አሳላም መስጅድ የሚፈለገውን ያህል ርቀት በመጠበቅ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን መከወን ላልቻሉ የእምነቱ ተከታዮች ነው ተብሏል።

ለዚህ ደግሞ በመስጅዱ በቂ ቦታ አለመኖሩ ምክንያት መሆኑ ነው የተነገረው።

ይህን ተከትሎም ማርታ ሉተርን ቤተ ክርስቲያን የእስልምና እምነት ተከታይ ምዕመናን የጁምዓ ጸሎት በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ እንዲደረግ ፈቃድ ሰጥታለች።

መስገጃ ቦታ ያገኙት ሙስሊም ምዕመኖችም ውሳኔው እንግዳ ስሜት እንደፈጠረባቸውና እጅግ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።

በሃገሪቱ ከሳምንታት በፊት የ1 ነጥብ 5 ሜትር አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ሃይማኖታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ መፈቀዱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.