Fana: At a Speed of Life!

በጃፓኗ ቶኪዮ በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተሰማ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሊምፒክ ውድድር አስተናጋጇ ቶኪዮ በአንድ ቀን 3 ሺህ 177 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸውን የከተማዋ ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡

በከተማዋ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመርም በሆስፒታሎች ላይ ጫና ማሳደሩ ነው የተገለጸው፡፡

በቶኪዮ አቅራቢያ በሚገኙት ካናጋዋ፣ ቺባ እና ሳኢታማ ግዛት አስተዳዳሪዎችም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ መንግስትን እንደሚጠይቁ ገልጸዋል፡፡

ከቫይረሱ መስፋፋት ጋር ተያይዞም ቀጣይ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ያለተመልካች ሊካሄዱ ይችላሉ ነው የተባለው፡፡

ባሳለፍነው ማክሰኞ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂዴ ሱጋ ዜጎቻቸው በቤታቸው ሆነው የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን እንዲከታተሉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በቅርብ ጊዜ በኦሊምፒክ መንደሩ አካባቢዎች ላይ በተደረገ የኮቪድ19 ምርመራ 16 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በጃፓን በአንድ ቀን ከዘጠኝ ሺህ በላይ አዳዲስ የኮቪድ19 ተጠቂዎች መገኘታቸውን የሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.