Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ ህገወጥ የጦር መሳርያዎችና 14 ሺህ ሃሰተኛ የብር ኖቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ የተለያዩ ህገወጥ የጦር መሳርያዎች ጨምሮ 14 ሺህ ሃሰተኛ የብር ኖቶች መያዛቸውን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ኮማንደር ፉፋ መገርሳ አስታወቁ።
ኮማንደር ፉፋ መገርሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የከተማውን ፀጥታ ለማስከበር ሰሞኑን በተደረገ ብርበራ የተቀበሩ የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ ሀሰተኛ የብር ኖቶች መያዝ ተችሏል።
ከተያዙት መሳሪያዎች መካከልም÷ 2 ክላሽ፣ 5 ሽጉጥ፣ 100 የክላሽና 5 የብሬን ጥይቶች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
በተጨማሪ ተቀብረው የዛጉና ተሰባብረው ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ መሳርያዎችም ተይዟል ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ በጅማ ከተማ አገልግሎት ላይ ሊውሉ የነበሩ 14 ሺህ 200 ሃሰተኛ የብር ኖቶች በህብረተሰቡ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ኮማንደር ፉፋ አስታውቀዋል።
ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ÷ የከተማው ነዋሪዎች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጎን ሆነው የከተማውን ሰላም ለማስከበር እያደረጉት ያለው ን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.