Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ ለ1 ሺህ 954 ሰዎች የስራ ዕድል ተፈጠረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ በ335 ማኅበራት ስር ለተዳራጁ የከተማው ነዋሪዎች በከተማ ፅዳት፣ በንግድ፣ አካባቢን በማስዋብ እና በግብርና ሥራ የስራ እድል ተፈጠረላቸው።
የሥራ ዕድል ለተፈጠራላቸው የከተማዋ ነዋሪዎችም ÷ 50 ሼዶች፣ 3 የክላስተር ሼዶች፣ 5 ትራክተሮች እና የተለያዩ የፅዳት መሳርያዎች እንደተሰጠ ነው የተገለጸው፡፡
የከተማው የሥራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የዚድ አባ ገሮ ÷ የጅማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በአዌቱ ወንዝ ዳር የለሙ ቦታዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 300 ሚሊየን ብር የወጣባቸው የሥራ ቦታዎችንና ማሽነሪዎችን ነው የሥራ እድል ለተፈጠረላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ማስተላለፋቸውን የተናገረው፡፡
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ነጂብ አባ ራያ በበኩላቸው፥ የሥራ እድል የተፈጠረላቸው ሰዎች ተግተው በመስራት እራሳቸውን ለውጠው ለሌሎችም የስራ እድል እንዲፈጥሩ ነው ያሳሰቡት፡፡
በማኅበር ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ የከተማው ነዋሪዎች የሼዶችና የትራክተር ቁልፍ ከከንቲባው ተረክበዋል።
በሙክታር ጠሃ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.