Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ በከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 36 ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በጅማ ከተማ ከ551 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 36 ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡
በምረቃ ስነ ሥርዓቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ እና ሌሎች የክልልና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ የአዌቱ የወንዝ ዳር ልማትና የእግረኛ ሟቋረጫ መንገድ፣ የመንገድ ዳር መብራት፣ የትፊክ መብራት፣ የገበያ ማዕከል እንዲሁም ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤትን የሚያካትቱ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ 36 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ ተገልጿል።
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ነጂብ ራያ፥ ፕሮጀክቶቹ የከተማዋንና የአካባቢዋን ነዋሪዎችን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልሱ ከመሆናቸው ባለፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ በመንግስት በጀት፣ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፥ በክልል ደረጃ 20 ሺህ ፕሮጀክቶች እንደሚመረቁ አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም የክሉ ከተሞች እድገታቸውን ለማረጋጥ÷ ገቢ ማሳደግ ላይ፣ ሙያናና ክህሎት እንዲሁም የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

 

በሙክታር ጣሃ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.