Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ወደመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ የወረዳ ሁለት ጽህፈት ቤት ዋና አዛዥ ኮማንደር ካሊድ አባ ተማም ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው ዛሬ ንጋት 11 ሰዓት ከ30 ደቂቃ አካባቢ መድረሱን ለኢዜአ ተናግረዋል።

በከተማዋ በቦቾ ቦሬ ቀበሌ መናኸሪያ አካባቢ በሚገኝ አንድ የእንጨት ስራ ወጤቶች ማምረቻና መሸጫ የግል ድርጅት ላይ አደጋው ደርሷል ብለዋል።

በአደጋው በድርጅቱ ተመርተው ለገበያ የተዘጋጁ ዘመናዊ የእንጨት ስራ ውጤቶች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን አመላክተዋል።

“የወደመው ንብረት 6 ሚሊየን ብር ግምት አለው” ያሉት ኮማንደር ካሊድ በአደጋው በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ተናግረዋል።

በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በጸጥታ አካላትና በእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች ትብብር በተደረገ ጥረት ቃጠሎው ወደ ሌሎች የንግድ ተቋማት ሳይዛመት በቁጥጥር ስር መዋሉንም ጠቁመዋል።

እንደ ኮማንደር ካሊድ ገለጻ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.