Fana: At a Speed of Life!

በጆርጂያ ግዛት ዳግመኛ በተካሄደው የድምጽ ቆጠራ ጆ ባይደን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካዋ ጆርጂያ ግዛት ዳግመኛ በተካሄደ የድምጽ ቆጠራ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ማሸነፋቸው ተረጋገጠ፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጆርጂያ ግዛት የተካሄደው ምርጫ ተጭበርብሯል በማለት ክስ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው ድምጽ ዳግመኛ የተቆጠረው፡፡

በውጤቱም ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በ12 ሺህ 284 የድምጽ ብልጫ ነው ማሸነፋቸው ይፋ የሆነው፡፡

ባይደን ከውጤቱ በኋላ ዴሞክራሲን በተመለከተ ትራምፕ ለዓለም እያስተላለፉት ያለው መልዕክት አደገኛ ነው ብለዋል፡፡

በአሜሪካ ታሪክም ሃላፊነት የማይሰማው ፕሬዚዳንት ነው በማለትም ወርፈዋቸዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ በሦስት ግዛቶች በጆርጂያ፣ በፔንሲልቫንያ እና በአሪዞና ያቀረቡት ክስ ውድቅ ሆኖባቸዋል፡፡

ሆኖም ዶናልድ ትራምፕ አሁንም ቢሆን በምርጫው መሸነፋቸውን አላመኑም ነው የተባለው፡፡

እስካሁን በሁሉም ግዛቶች በተካሄደው የድምጽ ቆጠራ ባይደን በ5 ነጥብ 9 ሚሊየን ብልጫ አላቸው ተብሏል፡፡

እንዲሁም ወሳኝ በሆነው የግዛቶቹን ውክልና በሚይዘው ድምጽ ደግሞ ባይደን 306 ድምጽ ሲይዙ ትራምፕ 232 ድምጽ ነው ያገኙት፡፡

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በታህሳስ ወር 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን ወደ ኋይትሐውስ እንደሚያመሩ ይጠበቃል፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.