Fana: At a Speed of Life!

በገላን ከተማ ለሚገነቡ ትምህርት ቤቶች የግንባታ ማስጀመሪያ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በገላን ከተማ ለሚሰሩ ትምህርት ቤቶች የግንባታ ማስጀመሪያ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡
በዛሬው ዕለት የግንባታ ማስጀመሪያ መሰረተ ድንጋይ የተቀመጠላቸውም ለኢፈ ቦሩ ቢቴ እና ጨፌ ቱማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነው፡፡
በፕሮግራሙ ላይ በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ተገኝተዋል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ በ35 ሚሊየን ብር በ24 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነቡ መሆኑን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡
የክልሉ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የመማሪያ ክፍሎችን እጥረት ለመቅረፍ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በኢፈ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ እና ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በዕቅድ ከተያዙት 19 ግንባታ ላይ እንደሚገኙ የቢሮው ኃላፊ ገልፀዋል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.