Fana: At a Speed of Life!

በገና በዓል በቱሪስቶች የምትጨናነቀው የቤተልሄም ከተማ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ ቁጥር ያላቸው ቱሪስቶች እየሱስ ክርስቶስ የተወለደበትን ቀን ለማክበር ወደ ቤተልሔም  ከተማ ያቀናሉ፡፡

በዛሬው ዕለትም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ ተጓዦች እና ቱሪስቶች በእስራኤል እየሱስ ክርስቶስ በተወለደባት ቤተልሔም  ከተማ  ገናን በማክበር ላይ ይገኛሉ ፡፡

በዘንድሮው ዓመት በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የተሰባሰቡ ሰዎች ቁጥር ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃጸም ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።

በዚህ መሰረትም 1 ነጥብ 9 ሚሊየን የሚሆኑ ቱሪስቶች በዓሉን በማስመልከት ወደ ስፍራው ማቅናታቸው ተገልጿል።

በዓለም ዙሪያ የአውሮፕውያኑን የዘመን አቆጣጠር የሚጠቀሙ ሀገራት የእየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓልን  በዛሬው ዕለት እያከበሩ ነው።

ምንጭ፣ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.