Fana: At a Speed of Life!

በገና ኤግዚብሽንና ባዛር ለዲያስፖራው ጥራቱን የጠበቀ ምርት ይቀርባል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በመዲናዋ በተመረጡ በከተማና በሁሉም ክፍለ ከተሞች የ2014 የገና ኤግዚብሽንና ባዛር ከሌላው ጊዜ በተለየ ጥራት እንደሚካሄድ የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ገልጿል፡፡

የገና ኤግዚብሽንና ባዛሩም  ከታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ ነው የተገለፀው፡፡

በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኢንተርፕራይዝ ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ ÷  ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ከ1 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች  ጥራት ያለው የሀገር ባህልና የፍጆታ ዕቃዎችን ከኢንተርፕራይዞችና ከኢንዱስትሪዎች እንዲሸምቱ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ኤግዚብሽንና ባዛሩ በዋናነት በወዳጅነት አደባባይ፣ በእንጦጦ ፓርክ፣ በኢትዮ ኩባ አደባባይ፣ በአምባሳደር ፓርክ፣ በፕላዛ፣ በመቻሬ ሜዳና በከተማው በተመረጡ ቦታዎች በታላቅ ድምቀት እንደሚካሄድ ኃላፊው መግለፃቸውን ኢንተርፕራዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ  ያመላክታል፡፡

በኤግዚብሽንና ባዛሩ ሀገራዊ አንድነትን፣ አሸናፊነትን ሀገራዊ አሁናዊ ሁኔታን ከፍ በሚያደርጉ መርሃ ግብሮች ታግዞ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ታቅዷል፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.