Fana: At a Speed of Life!

በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በኩዌት ጉብኝት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በኩዌት ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከኩዌቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ሼክ ሳባህ ካሊድ አልሃምድ አልሳባህ ጋር በኢትዮጵያና በኩዌት የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ፍሪያማ ውይይት ማድረጋቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ በኩል ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን÷ በኩዌት በኩል ደግሞ የነዳጅና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሞሀመድ አልፋሬስ፣ የገንዘብ ሚኒስትርና የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ካሊፋ ሃማዳ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና አማካሪ አብዱል አዚዝ አልዳኬል ተገኝተዋል፡፡
የኩዌት ጠቅላይ ሚኒስትር ሼኪ ሳባህ ካሃሊድ አልሃማድ አልሳባህ በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ኩዌት ሲገባ በባያን ቤተ መንግስት አቀባበል አድርገውለታል፡፡
በአቀባበል ስነ ስርአቱ የኩዌት የነዳጅና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሞሃመድ አል ፋሪስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችም መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.