Fana: At a Speed of Life!

በገንዘብ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ በደቡብ ወሎ የደረሰዉን ጉዳት ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ ሚኒስትሮች የተካተቱበት ልዑክ በደሴና በሌሎች የደቡብ ወሎ ዞን አካባቢዎች በአሸባሪው የህወሃት ቡድን የደረሱ ጉዳቶችን ተመለከተ።
ልዑኩ የፌደራልና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ሲሆን፥ አሸባሪ ቡድኑ አካባቢዎቹን በወረራ ይዞ በነበረባቸው ቀናት ያደረሳቸውን ውድመቶች በመስክ ተንቀሳቅሶ ተመልክቷል።
በደቡብ ወሎ ዞንና ደሴ ከተማ አመራሮችም በጥፋት ቡድኑ የደረሰውን ጉዳት የሚያመላክት ሰነድ ቀርቦለታል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ በኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች ተዘዋውረው የተመለከቱት ጉዳት የአሸባሪ ቡድኑን ጭካኔና አገር አፍራሽነት በገሃድ ያሳየ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ለኀብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ የጤናና የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስባቸውም ወደ ሥራ እንዲመለሱ የተደረገውን ጥረት ማድነቃቸው ከደቡብ ወሎ ዞን ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.