Fana: At a Speed of Life!

በጉለሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ጉዳይ እንጨርሳለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚና ሌሎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 24 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ከመሬት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ቢሮው የሄዱ ተገልጋዮችን ጉዳይ እንጨርሳለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ የወረዳውን ስራ አስፈጻሚ እና የወረዳው ስነ-ምግባር መኮንን ያካተተ ቡድን በቁጥጥር ስር ውሏል።
 
በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ካሉት ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ከተዘረጋው ሰንሰለት በተጨማሪ ደላሎችም ይገኙበታል ነው የተባለው።
 
ለከንቲባ ፅህፈት ቤት በመጣ የተገልጋይ ጥቆማ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር በመተባበር ለአገልግሎት እንዲከፈላቸው የጠየቁትን ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
 
ህብረተሰቡም በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት ከተማ አስተዳደሩ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ጠቁሞ÷ ጥቆማውን ላደረሡን ተገልጋይ ያለንን ታላቅ አክብሮት እና ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል።
 
በመንግስት መዋቅር ውስጥ ተሠግስገው በአቋራጭ ገንዘብ በመቀበል በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት እንሠጣለን የሚሉ አካላትን በማጋለጥ ህብረተሠቡ ጥቆማውን በመስጠት ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል ።
 
የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በኩል በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረጉ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢሮ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.