Fana: At a Speed of Life!

በጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ሰዎችን በ15 ቀናት ውስጥ ወደቀያቸው ለመመለስ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 22 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጉራ ፈርዳ ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት  ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎችን በ15 ቀናት ውስጥ ወደ ቀያቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።

በጥቃቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች እስካሁን 6ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ መደረጉን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ተካልኝ ሽፈራው  ተናግረዋል።

ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣  ከመንግስት ተቋማት እና ከኃይማኖት ተቋማት የተሰበሰቡ የምግብ ፣ የአልባሳትና የማብሰያ ቁሳቁሶች ለተፈናቃዮች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

የአካባቢው ኗሪዎችና መንግስት እያደረጉት ባለው ድጋፍና ባሳዩት አጋርነት ደስተኛ መሆናቸውን ተፈናቃዮቹ  ገልጸዋል።

በወረዳው በተከሰተው ግጭት ከ5 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የገለጹት የወረዳው አስተዳዳሪ ÷ከሚደረገው ድጋፍ ባሻገር ተፈናቃዮችን በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወደቀያቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በግጭቱ ተሳታፊ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 12 አመራሮችን ጨምሮ 64 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤንች ሸኮ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ጊስካር ገልጸዋል።

በተስፋዬ ምሬሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.