Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ዙሪያ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ለተውጣጡ አመራሮች የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በክልሉ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የጤና አገልግሎት ሽፋን በተጠናከረ መልኩ መስፋፋቱም ለክልሉ የተቀላጠፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ያስችላል ብለዋል፡፡
በንቅናቄው ላይ ለተገኙት አመራሮች ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በታማኝነትና በትጋት እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮት ጋትዊች በበኩላቸው በከፍተኛ የመታከሚያ ወጪ ሳቢያ ኑሮ ሊጫነው የሚችለውን የህብረተስብ ክፍል በመታደግ የጤና አገልግሎትን በፍትሃዊነት ማግኘት እንዲችሉ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ በክልሉ የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን ፕሮግራምን ለመተግበር በጎደሬ፣ ላሬ እና ጎግ ወረዳዎች በሙከራ ፕሮግራም አገልግሎቱን ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.